በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ስርቆት በሚፈፅሙ ግለሰቦች ላይ የሚወሰደው የቅጣት እርምጃ ሊሻሻል ይገባል ተባለ

የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ ስርቆት እና ውድመት የሚፈፅሙ አካላት መረጃ  እና ማስረጃዎች ተገኝቶባቸው ለህግ ቢቀርቡም የሚወስደው የህግ እምጃ  ከሚያደርሰው ጉዳት አንፃር ተመጣጣኝ  እንዳልሆነ  የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሪክተር መላኩ ታዪ ለኢትዮኤፍኤም ተናግረዋል።

ከ60 እስከ 70 በመቶ የሚሆነው የኤሌክትሪክ  መሰረተ ልማት ግብአት ከውጭ በምንዛሬ በከፍተኛ በጀት ወደ ሀገር የሚገባ ሲሆን ፤ለደንበኞች  አስተማማኝ  አገልግሎት ለማድረስ እና ተደራሽነትን ለማስፋት ለሚደረገው ጥረት በሀገር ሀብት ላይ የሚደርሱ ስርቆች እና ውድመት እንቅፋት እንደሆነ ገልፀዋል።

በኢነርጂ አዋጁ ላይ እንደተቀመጠው ማንኛውም በመሰረተ ልማት ላይ ውድመት ያደረሰ አካል ከአምስት አመት እስከ 25 አመት ድረስ ሊቀጣ እንደሚገባ ይደነግጋል ያሉት ዳይሪክተሩ፤ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ውድመት እና ስርቆት የሚፈፅሙ አካላት በዋስ  እንዲሁም  አነስተኛ ፍርድ ሲፈረድባቸው ለሌሎች አስተማሪ አይደለም ብለዋል።

ህብረተሰቡም  የመሰረተ ልማቱን እንደ ግል ሀብቱ ተመልክቶ በዚህ እኩይ ተግባር ላይ እሚሳተፉ አካላትን ለህግ የማቅረብ ስራ ላይ ሊሳተፍ ይገባል ብለዋል።

እሌኒ ግዛቸው
ሚያዝያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.