በገለልተኛ አካል ሳይጣራ ከቅድመ ትንተናና ፍረጃ መቆጠብ ይገባል—ኢዜማ!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ግርማ የሺጥላ ከቤተሰቦቻቸው እና ጠባቂዎቻቸው ጋር በጉዞ ላይ እያሉ በተፈጸመባቸው ጥቃት በመገደላቸው የተሰማውን ሀዘን ገልጿል፡፡

የግድያው ምክንያት፣ ሂደት እና የገዳዮች ማንነት በተመለከተ በገልለተኛ አካል በሚደረግ ምርመራ በግልጽ ታውቆ ፍትሕ እስከሚሰጥ ድረስ፤ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጨምሮ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በግድያው ዙሪያ ትንተና፣ ፍረጃ እና የፖለቲካ ነጥብ ለማስቆጠር ከሚደረግ ሩጫ እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

እንዲህ አይነት የማኅበረሰቡን እሴት የሚንዱ መሰል ግድያዎችን በአንድ ድምጽ ልናወግዝ ይገባል ብሏል ኢዜማ።

ለሟቾች ቤተሰብ እና ወዳጅ ዘመድ በሙሉ መጽናናትን እንዲሁም በጥቃቱ ጉዳት አጋጥሟቸው የሕክምና ክትትል እያደረጉ ላሉት ፈጣሪ ምህረቱን እንዲሰጣቸው ፓርቲው ምኞቱን ገልጿል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሚያዝያ 20 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.