የቢቢሲ ሊቀመንበር በቦሪስ ጆንሰን የሙስና ቅሌት ምክንያት ከስልጣናቸዉ ለቀቁ፡፡

የቢቢሲ ሊቀ መንበር ሪቻርድ ሻርፕ የቀድሞ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስተር በነበሩት ቦሪስ ጆንሰን የሙስና ቅሌት ጋር በተገናኘ በፍቀዳቸዉ ከኃላፊነታቸዉ ተነስተዋል፡፡

ግለሰቡ ከሰሞኑ የቀድሞ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስቴር የሙስና ቅሌትን የሚገልጽ ዘገባ ከመውጣቱ በፊት ነው ስራቸውን መልቀቃቸው የታወቀው።

ሻርፕ በወቅቱ ከነበረው የቦሪስ አስተዳደር ካቢኔ ፀሐፊ ጋር በመሆን የሃገሪቱን አስተዳደራዊ መመሪያዎችን ጥሰዋል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም “ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስተር ቦሪስ ጆንሰን ገንዘብ በመቀበል፣ ፋይሎችን ሆን ብለው በማፋለስ ወንጀል ፈጽመዋል በሚል እንደተወነጀሉ አርቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡

በመሳይ ገብረ መድህን

ሚያዝያ 20 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.