በአዲስ አበባ በሱቆች እና በአዟሪዎች የሚሸጠው ማር በአብዛኛው ጤንነቱ ያልጠበቀ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

ጥናቱን ያደረጉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና የሆለታ የእንስሳት ምርምር ማዕከል በጋራ በመሆን ነው፡፡

ጥናቱም በአዲስ አበባ በስምንት ክፍለ ከተሞች የተካሄደ ሲሆን በሱቆች፣ በሱፕር ማርኬቶች እና በአዟሪዎች እጅ የሚገኙ የማር አይነቶች ለምርመራ በናሙናነት ተወስደዋል፡፡

በዚህ የምርመራ ውጤትም በአዲስ አበባ በሱቆች፣በሱፐር ማርኬቶችና አዟሪዎች እጅ ከሚገኘው ማር እስከ 80 በመቶ የሚሆነው የማር ምርት ጤንነቱ ያልጠበቀ መሆኑን ጥናቱ አሳይቷል፡፡

የሆለታ ንብ ምርምር እና ጥራት ማዕከል ተመራማሪ የሆኑት እና በጥናቱ የተሳተፉት አቶ ተረፈ ዳምጠው እንደተናገሩት፣ በአዲስ አበባ በገበያ ላይ የሚገኝው ማር የማይቀላቀልበት ባዕድ ነገር የለም ብለዋል፡፡

ከሱፕር ማርኬት አንስቶ እስከ አዟሪዎች ድረስ ያለው ማር ጤንነቱ ያልጠበቀ ከመሆኑ ባሻገር እጅግ ለከፋ የጤና ጉዳት ይዳርጋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በምርመራ እንደተረጋገጠው ስኳር፣ ሙዝ፣ የተፈጨ ጠርሙስ፣ ከረሜላዎች እና ሌሎችም ባዕድ ነገሮች እንደሚቀላቀሉበት አቶ ተረፈ ተናግረዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሚያዝያ 24 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.