እናት ባንክ “ለእናቴ” የተሰኘ ሁሉንም ማህበረሰብ ያሳትፋል የተባለ ሀገራዊ የጽሁፍ ዉድድር ጀመረ፡፡

ባንኩ በዛሬው እለት ለሀገርም ሆነ ለቤተሰብ ምሰሶ የሆኑ የኢትዮጵያ እናቶች መታሰቢያ እንዲሆን ለአንድ ወር የሚቆይ ሽልማት የሚያስገኝ “ለእናቴ” የተሰኘ የጽሁፍ ውድድር በይፋ አስጀምሯል።

ባንኩ በሰጠው መግለጫ የማወዳደርያ መስፈርቱ እና የውድድሩ ዳኝነቱ በቋንቋና በስነ-ፅሁፍ የካበተ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች እንደሚካሄድ ገልጿል፡፡

የማወዳደርያ መስፈርቱም የቅርፅ ጉዳዯች 50 በመቶ ፣ የይዘት ጉዳየች 50 ከመቶ በድምሩ 100 ነጥብ እንዲይዙ ተደርጎ መዘጋጀቱም ታውቋል፡፡
ውድድሩ ከዛሬ ሚያዚያ 26 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚቆይም ተጠቁሟል።

እናት ባንክ በአሁኑ ሰዓት ከ 2 ቢሊዮን ብር በላይ የተከፈለ ካፒታል ያለው ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 60 በመቶ የሚሆነው የባንኩ አክሲዮን በሴቶች ባለቤትነት የተያዘ ድርሻ መሆኑንም ኢትዮ ኤፍ ኤም በተሰጠው መግለጫ ላይ ሰምቷል፡፡

በረድኤት ገበየሁ
ሚያዝያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.