የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶች ዲጂታል መታወቂያ ለመውሰድ ፍላጎት እያሳዩ አይደለም ተባለ::

በአዲስ አበባ በአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ተመዝግበው የሚገኙ 18ሺህ እና በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ጂፒኤስ አስገጥመው የተመዘገቡ 11ሺህ የሚጠጉ የሞተር ብስክሌቶች መኖራቸውን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጀመንት ኤጀንሲ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ኩማ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ከዚህ ውስጥ 2 ሺህ የሚሆኑት ብቻ ናቸው ዲጂታል መታወቂያውን ያስቀየሩት ብለውዋል።
የተለያዩ ወንጀሎችን ለመፈፀም አመቺ የሆነውን ቀድሞ ለመንቀሳቀስ ሲጠቀሙበት የነበረው ወረቀታቸው የአብዛኞቹ ፎርጂድ( ህገ-ወጥ ) መሆኑንም ነግረውናል።

ለዚህም ወደ ዲጂታል ሲቀየር ከዚህ ቀደም ወንጀል ሰርተው የተመዘገቡትን እና አዲስ የህግ ጥሰት የተጠቆመባቸውን በቀላሉ አጣርቶ በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያስችል መሆኑን አንስተዋል።

ነገር ግን አብዛኛዎቹ ሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች በፎርጅድ እየተንቀሳቀሱ በመሆኑ፣ ወደ ዲጂታል ለመምጣት ፍላጎት እያሳዩ አለመሆኑን ለጣቢያችን ተናግረዋል።
መታወቂያው ጂፒኤስ ያስገጠመ እና ያላስገጠመን የሚለይ ፣ የመንቀሳቀሻ ፈቃዱ ህገ-ወጥ ነው ኦርጂናል የሚለውን ጨምሮ የታደሰ ነው ያልታደሰ እንዲሁም ከዚህ ቀደም የህግ ጥሰት ፈፅሟል አልፈፀመም የሚለውን የሚለይ ነው ሲሉ አቶ ብርሃኑ ነግረውናል።

ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እስከ ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የቀድሞ መታወቂያቸውን በዲጂታል እንዲያስቀይሩ የተራዘመ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ከግንቦት 10 በኋላ ግን ቁጥጥር ይጀመራል ብለዋል።

በረድኤት ገበየሁ
ግንቦት 01 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.