በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ በኮሌራ በሽታ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነግሯል፡፡

በደቡብ ክልል በአማሮ ልዩ ወረዳ በተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ ምክንያት የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የልዩ ወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል ።

በጽ/ቤቱ የበሽታ መከላከል እና ጤና ማጎልበት ዋና የስራ ሂደት መሪ አቶ አክሊሉ ካሌብ እንደተናገሩት ከወረዳው አጎራባች ቦታዎች በመጡ ሁለት በበሽታው በተጠቁ ግለሰቦች ምክንያት በሽታው ሊዛመት ችሏል ።

በተለይ በወረዳው በርካታ ሰዎች በሚንቀሳቀሱባቸው ይሮ፤ቂሲ ማሼ እና ቤዚ ማሼ ቀበሌዎች በሽታው በፍጥነት እየስፋፋ ነው ብለዋል።

አሁንም በአጎራባች ዞኖችና እና በልዩ ወረዳው መካከል ያለው ማህበራዊ መስተጋብ የጠነከረ መሆኑ በሽታውን ለመከላከል ፈታኝ እንደሚያደርግባቸው ገልፀዋል ።

በተጨማሪም በልዩ ወረዳው የሚስተዋለው የመድኃኒት እጥረት የወረርሽኙን አስጊነት ከባድ እንደሚያደርገው አንስተዋል ።

አሁን ላይ የወረርሽኙን የመዛመት ፍጥነት ለመለየት አስቸጋሪ እንደሆነባቸው የተናገሩት አቶ አክሊሉ ወረዳው በተቻለ አቅም የግንዛቤ ስራዎችን ለመስራት የጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎችን ማሰማራቱን ገልጸዋል ።

ጉዳዩንም ለደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ማሳወቃቸውን የገለፁት ባለሞያው በዛሬው እለት ከክልሉ የተላኩ የሉካን ቡድኖች ይገባሉ ብለው እንደሚጠብቁ ነግረውናል ።

እስካሁን ድረስ በተረጋገጠው መረጃ መሰረት በርካታ ሰዎች በበሽታው ሲያዙ የአራት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን ገልጸው ቁጥሩ ከዚህ በእጅጉ ሊበልጥ ይችላል ብለዋል ።

መሳይ ገ/መድህን
ግንቦት 03 ቀን 2015

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *