ቴክኖ ሞባይል አዲስ የስፓርክ 10 ሲሪየስ ስልክ በኢትዮጵያ ይፋ አደረገ፡፡

ቴክኖ ሞባይል ስፓርክ 10 የተሰኝ አዲስ የሞባይል ስልክ ምርት በይፋ አስመርቋል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ70 በላይ ዓለምአቀፍ ገበያዎች ላይ በተጠቃሚዎች ዘንድ ተቀባይነትን ያተፈራው ቴክኖ ሞባይል፣ ለሁለት ቀናት በሚቆየው ዝግጅት የስፓርክ 10፣ ስፓርክ 10ሲ እና ስፓርክ 10 ፕሮ ሞዴሎች ለገበያ ማቅረቡን አስታውቋል።

ስልኮቹ የተጠቃሚውን ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት ዘመናዊ የፊት ለፊት ካሜራን፣ ወቅታዊ ዲዛይን እና ፈጣንና ፕሮሰሰር በመጠቀም ለተገልጋዮች መቅረቡን ገልጿል።
ስፓርክ 10 ሲሪየስ ስልክ ሞዴል ስልኮች ድንቅ ምስሎችን እንዲያነሱ ታስቦ የተሰሩ ናቸው ተብሏል።

ትራንስሚሽን ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር (ቴክኖ ሞባይል) ጎሮ አካባቢ በሚገኘው አይሲቲ ፓርክ ያስገነባው ዘመናዊ ፋብሪካ፣ ባለፉት ዓመታት የተለያዩ ዓይነት የስልክ ምርቶችን በመገጣጠም ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ገበያዎች ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወቃል።

ይህንን ዘመናዊ ፋብሪካ በመጠቀም ስልኮችን ለገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬን ያስቀረ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ የወጪ ንግድ ገቢ ማሰገኝት መቻሉም ተነግሯል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ቋሚ የስራ እድል መፍጠር መቻሉን አስታውቋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርአኤል

ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *