ከግል ጉዳዩ ጋር በተያያዘ የወረዳ ስራ አስፈፃሚውን የገደለ የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገለጸ፡፡

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ የእለት ከእለት ተግባራቸውን በማከናወን ላይ እንዳሉ ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ/ም ማለትም ዛሬ ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ በፖሊስ አባል ተገድለዋል፡፡

ግድያውን የፈፀመው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የካሳንቺስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የቀጠና ኦፊሰር የሆነ አባል የግል ጉዳዩ እንዲፈፀምለት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለወረዳ 8 አስተዳደር ጽ/ቤት ያመለክታል፡፡

ወረዳው ጉዳዩን ተመልክቶ ምላሽ እንደሚሰጠው የተገለፀለት ቢሆንም ጥያቄዬ እንዳይፈፀም የከለከልከው አንተነህ በሚል ምክንያት የወረዳውን ዋና ስራ አስፈፃሚ ቢሯቸው ውስጥ በስራ ላይ እንዳሉ በታጠቀው ሽጉጥ መግደሉ ታውቋል ብሏል ፖሊስ፡፡

ወንጀሉን የፈፀመው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው እየተጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

የፖሊስ አባሉ በፈፀመው ድርጊት ማዘኑን በመግለፅ ለሟች ቤተሰቦች ፣ ጓደኞችና የስራ ባልደረቦች መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.