የተርኪዬ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ ባለማግኘቱ ድጋሜ ሊካሄድ ነዉ፡፡

በፕሬዝዳንት ረሲጵ ታይጵ ኤርዶሃንና በተፎካካሪዎችቻቸዉ መካከል ያለዉ ግድድር አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል፡፡

በትናትናዉ እለት አሸናፊዉ ይለይበታል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረዉ የተርኪዬ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ኤርዶሃንም ሆኑ ተቀናቃኞቻቸዉ ስልጣን ላይ ሊያስቀምጥ የሚያስችል ድምጽ ባለማግኘታቸዉ ምርጫዉ በቀጣይ ግንቦት 28 በድጋሜ እንዲካሄድ ተወስኗል፡፡

የአገሪቱ የምርጫ ጠቅላይ ምክር ቤት ሊቀምንበር እንዳስታወቁት ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን በመጀመሪያው ዙር ምርጫ የ49.51 በመቶ የመራጮች ድምጽ አግኝተዋል።

ምንም እንኳን ተፎካካሪያቸው ከማል ኪሊችዳሮግሉ የ44.88 በመቶ መራጮችን ድምጽ በማግኘት በኤርዶዋን ቢበለጡም ሁለቱም ዕጩዎች ለአሸናፊነት የሚያበቃውን ከግምሽ በላይ ድምጽ አላገኙም።

ሁለተኛው ዙር ምርጫ ከሁለት ሳምንት በኋላ የሚካሄድ ሲሆን፣ በዚህም ኤርዶሃን የማሸነፍ ዕድል እንዳላቸው እየተነገረ ነው።

ባለፉት ዓመታት ተርክዬን የመሩት ረሲጵ ታይፕ ኤርዶሃን ትልቅ ስራ መስራታቸዉ ይነገራል፡፡
በተለይ በምጣኔ ሃብት፣ በሴቶች መብት፣ በዓለም አቀፍ ግንኙነት እና በሐይማኖት ረገድ የሚጠቀሱ ለውጦችን ማስመዝገብ እንደቻሉ የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ።

ዓለም አቀፍ የምርጫ ተቆጣጣሪ ቡድን (ኦኤስሲኢ) ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን እና ፓርቲያቸው ተገቢ ያልሆነ ተጠቃሚነትን አግኝተዋል በማለት በምርጫው ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችን መዘርዘሩን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡

የአልጄዚራዉ ኦማር ሃጂ ከተርኪየዋ ኢዝሚር ግዛት እንደዘገበዉ የኤርዶሃኑ ኤኬ ፓርቲ ትልቅ ፈተና ገጥሞታል ብሏል፡፡
የኤኬ ፓርቲ በፓርላማ ያለዉ ቦታ ከ296 ወደ 266 እንደቀነሰበትም ኦማር ሃጂ ጽፏል፡፡
ስለቀጣዩ ምርጫ ተፎካካሪ ዎቹ ምን አሉ ለሚለዉ ፤ ኤርዶሃንም ሌሎቹም በጉጉት እንጠብቀዋን፤ እናሸንፋለን የሚል ተስፋ ማንገባቸዉን አልጄዚራ ዘግቧል፡፡

ለመሆኑ የግንቦት 28ቱ ዳግም ምርጫ ኤርዶሃንን ከስልጣን ያስወርዳል ወይስ በዙፋናቸዉ ቀጥለዉ ተርክየንም እራሳቸዉን በአለም ፖለቲካ አትሮኖስ ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ አድርገዉ ይቀጥሉ ይሆን የሚለዉ የበርካቶች ጥያቄ ነዉ፡፡

በርካታ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ ኤርዶሃን የቀጣዩን ምርጫ በበላይነት ይወጣሉ እያሉ ነዉ፡፡

የፖለቲካ ተንታኙ አሊ ካርኮግሉ አሁንም ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን ከተፎካካሪዎች ይበልጥ በመላ ሀገሪቱ በተለይም በአናቶሊያ፤ በደቡባዊ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል በርካታ ደጋፊዎች አሏቸዉ ነዉ ያሉት፡፡

በቅርቡ ተርኪዬ በከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ መመታቷ የሚታወስ ሲሆን በወቅቱም በተለይም አደጋዉ እንደደረሰ የኤርዶሃን መንግስት አስቸኳይ እርዳታ አላደረገም በሚል ትችት ሲቀርብበት ነበር፡፡

እንዲሁም የኮንስትራክሽን ዘርፉም ደካማ ነዉ በሚል ሲወቀስ ነበር፡፡
ታዲያ ይህ አጋጣሚ ደግሞ በአሁኑ ምርጫ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድርባቸዉ ይችላል ሲባ ነበር፡፡

ይሁን እንጅ አደጋዉ ከደረሰ በኋላ ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን ተገቢ የሆነ ድጋፍ አድርገዋል ይላሉ ተንታኙ አሊ፡፡እናም በአሁኑ ሰኣት ከኤርዶሃን የተሸለ ሰዉ ለአንካራ የለም ነዉ ያሉት፡፡

የአልጄዚራዋ ዜይና ኮዲሂር በርካታ ተርክዬዎች ለኪሊዳሮግሉ ድምፅ በመስጠታቸዉ ተፀፅተዋል ብላለች፡፡

የኩርድ አፍቃሪያን ናቸዉ የሚል ክስም በኤርዶሃን መንግስት ይከሰሳሉ፡፡

በአባቱ መረቀ
ግንቦት 08 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *