ዩክሬን 18 የሩሲያ ሚሳኤሎችን መታ መጣሏን አስታወቀች።

በዩክሬኗ መዲና ኬይቭ ላይ ጥቃት ሊሰነዝሩ የነበሩ 18 የሩሲያ ሚሳኤሎችን ማዉደሙን የሀገሪቱ ጦር አስታዉቋል፡፡

ሩሲያ በዩክሬን ከተሞች ላይ መጠነ ሰፊ የሚሳኤልና የድሮን ጥቃቶችን መክፈቷ ተሰምቷል፡፡

የዩክሬን አየር ኃይል በበኩሉ ጥቃቱን እየተካለከለ ሚሳኤሎችንም መቶ መጣሉን ነዉ ያሳወቀዉ፡፡

የሞስኮ ጠር በኬይቭ ሰማይ ላይ በወሰደዉ ጥቃት ሶስት ሰዎች መጎዳታቸዉን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል፡፡

ሩሲያ በዩክሬኗ መዲና የጀመረችዉ የአየር ላይ ጥቃት የግንቦት ወር ከገባ ወዲህ ለ8ኛ ጊዜ የተደረገ ስለመሆኑም ዘገባዉ ጠቅሷል፡፡

የዩክሬን ባለስልጣናትም የሩሲያን ጥቃት እያከሸፍን ነዉ ብለዋል፡፡

በአባቱ መረቀ

ግንቦት 08 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.