ፍሊንትስቶን ሆምስ የአክሲዎን ሽያጭ ሊጀምር ነው፡፡

ፍሊንትስቶን ሆምስ ከሐምሌ 1 ቀን 2015 ጀምሮ የአክሲዎን ሽያጩን ሊያካሄድ መሆኑን ገለጸ፡፡

አክሲዮኑ ከ 20 ሺህ እስከ 2 ሚሊየን ብር ድረስ ለሽያጭ መቅረቡን የፍሊንት-ስቶን ሆምስ ባለቤት ኢንጅነር ፀደቀ ይሁኔ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል።

የአክሲዮን ሽያጩ ድርጅቱ የሚያቀርባቸውን ቤቶች በተመጣጣኝ እና በአስተማማኝ መንገድ ለደንበኞች ማቅረብ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግም ተነግሯል።

በሚቀጥሉት አምስት አመታት 10 ሺህ ቤቶችን ለደንበኞች የማቅረብ እቅድ እንዳለውም ነው የተገለፀው፡፡
ከሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ 10 ሚሊዮን አክስዮኖችን ለሽያጭ ማቅረቡንም አስታውቋል፡፡

አክሲዮን ገዢዎች በገዙት የአክሲዮን ገንዘብ መጠን አክሲዮናቸውን ወደ ቤት መቀየር እንደሚችሉም ተመላክቷል።

በ1984ዓ.ም የተቋቋመው ፊሊንትስቶን ሆምስ በመላ ሃገሪቱ በልዮ ልዮ የመሰረተ ልማት ገበያ ላይ ሲንቀሳቀስ የቆየ ሲሆን፤ከ15 አመት በፊት በቤቶች ልማት ገበያ ላይ ከተቀላቀለ በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ ደንበኞችን የቤት ባለቤት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ድርጅቱ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ግንቦት 08 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.