የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት በቡድን ሰባት አባል ሃገራት ጉባዔ ላይ እንደሚሳተፉ ተነገረ፡፡

ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘሌንስኪ በጃፓኗ ሄሮሺማ ከተማ ዛሬ በሚጀምረዉ የቡድን ሰባት ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ላይ በአካል እንደሚገኙ ታዉቋል፡፡

ቀደም ሲል ዘሌንስኪ አሁን ካለዉ የፀጥታ ሁኔታ አንፃር ወደ ጃፓን እንደማይጓዙ የተነገረ ቢሆንም፣ ሩሲያ ላይ ጫና ለማሳደር በአካል እንደሚገኙ ተረጋግጧል፡፡

የቡድን ሰባት አባል ሀገራት መሪዎች በሩሲያ ላይ ጠንከር ያለ ማእቀብ ለመጣል በጃፓኗ ሄሮሺማ ተሰባስበዋል፡፡

ሀገራቱ ከሩሲያ በተጨማሪ ቻይና ላይም መጠነ ሰፊ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ይጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል የዘገበዉ አልጄዚራ ነዉ፡፡

በአባቱ መረቀ
ግንቦት 11 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.