በመንግስት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ በሚደረጉ መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ተጠቃሚው ደሃው ማህበረሰብ አይደለም ተብሏል፡፡

መንግስት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ በሚያደርጋቸው እቃዎች እየተጠቀመ ያለው ዝቅተኛ ገቢ ያለው ማህበረሰብ አይደለም ሲሉ በገንዘብ ሚኒስቴር የታክስ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ዋሲውን አባተ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

መንግስት የኑሮን ጫናን ለማቅለል በሚል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ነዋሪዎች የሚጠቀሙትን መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን ከተጨማሪ እስት ታክስ ነጻ እያደረገ ይገኛል ፡፡

ነገር ግን በዚህ የሚጠቀመው ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማህበረሰብ ሳይሆን ሃብታሙ ነው ብለዋል፡፡

ለዚህ ደግሞ መነሻ ምክኒያቱ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘውን እና ሌላውን ማህበረሰብ ሳይለይ በጥቅል የሚደረግ ድጋፍ መሆኑን ተናግረዋል ።

ይህ ደግሞ መንግስትን ከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ እንደሚከተው አቶ ዋሲውን አንስተዋል ።

የተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የመደረጉ አለማው ደሃውን ማህበረሰብ መደገፍ ቢሆንም ተጠቃሚው ግን የመግዛት አቅም ያለው ማህበረሰብ መሆኑን ገልጸዋል

ስለሆነም መንግስትን ከኪሳራ ለመታደግ እና ተገቢው አካል ለመደገፍ ፣እገዛ የሚያስፈልገውን የማህበረሰብ ክፍል ቀድሞ መለየት ተገቢ ነው ብለዋል ።

ለዚህም ደግሞ አዲስ የተቀረጸው የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ነግረውናል ።

በመሳይ ገ/መድህን
ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.