የመንግስት ተሸርካሪዎችን ጨምሮ ባልተፈቀደላቸው መንገድ ላይ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ 7ሺህ አሽከርካሪዎች ላይ እርመጃ መወሰዱ ተገለፀ፡፡

ለባስ ብቻ ተብሎ በተለየው መንገድ ላይ ከታለመለት ዓላማ ውጭ በርካታ ተሸከርካሪዎች እየተጠቀሙት መሆኑን ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡

የመንግስት ተሸከርካሪዎችን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ተሸከርካሪዎች ከተፈቀደላቸው መስመር ውጪ ለባስ ብቻ ተብሎ በተለየ መንገድ ላይ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ 7ሺህ አሽከርካሪዎችን የመቅጣቱን ስራ ኤጀንሲው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል፡፡

የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር እና ሁነት አስተዳዳር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ጌታቸው ለጣብያችን እንደገለፁት ከሆነ በከተማዋ በተለዩ አምስት ቦታ ዎች ላይ የተለየ ለባስ ብቻ መንገድ ባማዘጋጀት ፍሰቱን ለማስተካከል እየተሰራ ቢገኝም ይህንን ሂደት በማወክ ላይ ያሉ ተሸከርካሪዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው ብለዋል፡፡

የመንግስት ተሸከርካሪዎች በበርካታ ግዜ መንገዱ ለነሱም እንደተፈቀደ በማስመል ቢንቀሳቀሱም ታርጋ በመመዝገባ ተቋማቸው ድረስ ድብዳቤ በመላክ የመቅጣት ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡

ኤጀንሲው ማንኛውም ተሸከርካሪ ከተፈቀደላቸው አውቶብስ እና ሚዲ ባስ ውጪ በሰዓት ገደቡ መሠረት ከጠዋቱ 12 እስከ 3 ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 10 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ባለው ለባስ ብቻ ተብሎ በተለየ መንገድ ላይ ሲንቀሳቀስ የተገኘ ማንኛውም መኪና እርማጃ ይወሰድበታል ሲል ለጣብያችን አስታውቋል፡፡

አቤል ደጀኔ
ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *