አደጋዉ ያደረሰዉ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 47681 የሆነ የቤት አዉቶሞቢል ሲሆን አደጋዉን የደረሰዉ ደግሞ መንገድ ሲጠቀሙ በነበሩ እግረኞች ላይ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸዉ ሁለት ተጎጂዎች ወዲያዉኑ ወደሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን ሌላኛዉ የ35 ዓመት እግረኛ በተሽከርካሪዉ ተገጭቶ 20 ሜትር ርቀት ወዳለዉ ገደልና ወንዝ ዉስጥ የገባዉ ሰዉ ህይወቱ አልፏል።
ህይወቱ ያለፈዉን ሰዉ አስከሬን ከትላንት ምሽት ጀምሮ ፍለጋ ሲያካሂዱ የነበሩት የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጠላቂ ዋናተኞች አስከሬኑን 20 ሜትር ርቀት ካለዉ ገደልና ወንዝ ዉስጥ አስከሬኑን አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም











