ካናዳ እና ሳዑዲ አረቢያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸዉን ለመመለስ ተስማሙ፡፡

በፈረንፎቹ 2018 ከተፈጠረዉ እና በሁለቱ አገራት መካከል ያለዉን የንግድ እና የስራ ግንኙነት ካሻከረዉ ግጭት በኋላ፣ሃገራቱ በድጋሚ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸዉን ለመመለስ ተስማማተዋል፡፡

ሙሉ በሙሉ የነበራቸዉን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመመለስ እና አምባሳደሮችንም ለመሾም መስማማታቸዉን ነዉ ሮይተርስ የዘገበዉ፡፡

ከሁለቱም ሃገራት የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ ሁለቱ አገራት እዚህ ስምምነት ላይ የደረሱት ባለፈዉ አመት ህዳር ላይ በተካሄደዉ የእስያ ፓስፊክ የኢኮኖሚ ትብብር መድረክ ላይ የአገራቱ መሪዎች በግላቸዉ ባደረጉት ምክክር ነዉ ተብሏል፡፡

መረጃዉ አክሎም ይህ ዉሳኔ የመነጨዉ ሁለቱ አገራት በመከባበር እና በጋራ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲኖራቸዉ በመፈለጋቸዉ ነዉ ብሏል፡፡

የካናዳ ዉጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሜላኒ ጆሊ በበኩላቸዉ ‹‹ ለአለም አቀፍ ችግሮች አለምአቀፋዊ መፍትሄ የምንፈልግ ከሆነ አንዳንዴ በሁሉም ነገር መስማማት ከማንችላቸዉ ሰዎች ጋር መነጋገርም አስፈላጊነዉ›› ሲሉ መግለጻቸዉን የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.