ከንቲባው ፤ ” ክለባችን ባህር ዳር ከነማ በዘንድሮው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ ዋንጫ ለማንሳት እየተፎካከረ ይገኛል ” ብለዋል።
ይህንን መሠረት በማድረግ ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ከሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ጋር ለሚያደርገው ወሳኝ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች በርካታ ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጠው በአካል ተገኝተው ለመደገፍ ጉዞ ወደ ሀዋሳ ለማድረግ ዝግጅት ጨርሠው ወደ ተዘጋጀላቸው አውቶብስ እየገቡ ባሉበት ሁኔታ በተወረወረባቸው ቦንብ 23 የክለቡ ደጋፊዎች ቀላል እና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸዋል።
ከንቲባው ቦንቡን የወረወሩት ” ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ አካላት ” ናቸው ብለዋል።
ቀላልና ከባድ ጉዳት ያደረሰባቸው የክለቡ ደጋፊዎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ከንቲባው ገልጸዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም











