በሱዳን የሚገኘው የኢጣሊያ ኤምባሲ ወደ አዲስ አበባ ተዘዋወረ

በሱዳን የሚገኘው የኢጣሊያ ኤምባሲ ትናንት እሁድ ወደ አዲስ አበባ ተዛውሯል

በሱዳን ተቀናቃኝ ጄኔራሎች መካከል በቀጠለው ጦርነት ምክንያት ትላንት እሁድ ጣሊያን ኤምባሲዋን ወደ አዲስ አበባ ማዘዋወሯን አሳውቃለች፡፡

በሱዳን የኢጣሊያ አምባሳደር ሚሼል ቶማሲ ከስራ አጋሮቻቸው ጋር ትላንት እሁድ ጠዋት አዲስ አበባ ማረፋቸው ታውቋል፡፡

በካርቱም የሚገኘው የኢጣሊያ ኤምባሲ “በኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ውክልናችን በጊዜያዊነት ይመሰረታል” ሲል የኢጣሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

“አምባሳደር ቶማሲ እና ሰራተኞቻችን ከጊዜያዊ ጽህፈት ቤቱ ከአዲስ አበባ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ” ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ታጃኒ ናቸው፡፡

“ጣሊያን ለሱዳን የሰላም ጥረት የምታደርገውን አስተዋጽኦ በተሻለ ሁኔታ
እንቀጥላለን” ሲሉ መናገራቸውን መቀመጫውን ጣሊያን ያደረገው ANSA የተሰኘው የዜና ወኪል ዘግቧል ።

በያይኔአበባ ሻምበል

ግንቦት 21 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.