ዋና ለመዋኘት ወደ ወንዝ ውስጥ የገባ ወጣት ህይወቱ አለፈ፡፡

ትላንት ግንቦት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽት12:00 ሰዓት ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ቀርሳ እየተባለ በሚጠራዉ አካባባቢ በሚገኝ ወንዝ ዉስጥ ዋና ለመወኘት የገባዉ ዕድሜዉ 27 ዓመት የተገመተ ወጣት ህይወቱ አልፏል።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጠላቂ ዋናተኞች የወጣቱን አስከሬን ፍለጋ ሲያካሂዱ ቆይተዉ ዛሬ ግንቦት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ማለዳ 12 ሰዓት ላይ አስከሬኑን አግኝተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።

በአዲስ አበባና አካባቢዉ የዋና ችሎታ ሳይኖራቸዉ ዉሀ ባቆሩና በወንዞች ዉስጥ ዋና ለመዋኘት እየገቡ የሚሞቱ ታዳጊዎችና ወጣቶች እየተበራከቱ የመጡ ስለሆነ ታዳጊዎች ወጣቶች ዉሀ ባቆሩና ወንዝ አካባቢ ያላችሁን እንቅስቃሴ አቁሙ አቁሙ ሲል አዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳስቧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያ
ግንቦት 22 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.