ገዳ ባንክ አክሲዮን ማህበር እና ኦሮሚያ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ አርሶ-ደሮችን እና ባለሀብቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ስምምነቱ በኢንዱስትሪና በግብርና መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በሁለቱ ድርጅቶች መካከል በትብብር ለመስራት የተደረገ ነው።

የተደረገው ስምምነት የሀገሪቷን አርሶአደሮችን ፣የሃገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶችን በማገዝ የግብርና ምርቶችን በጥራትና በብዛት ለኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲያውሉ የሚረዳ መሆኑም ተገልጿል።

ለማህበረሰቡ የተሻለ የፋይናንስ አገልግሎት በመስጠት ኢኮኖሚያዊ መሻሻልን ከመደገፍ እና ከማስፋፋት አኳያ ስምምነቱ የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ታምኖበታል።

የገዳ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ቡልቱ እንዳሉት፣ገዳ ባንክ ለኮርፖሬሽኑ አጋሮች እና ለስራ ባልደረቦች የፋይናንስ አገልግሎት እንዲሁም አነስተኛ ፣መካከለኛና የረዥም ጊዜ ብድርና ልዩ ልዩ የብድር አይነቶችን ለመስጠትም ተስማምቷል።

የኢንዱስትሪያል ልማት ፓርኮች ኮርፖሬሽኑ፣ ባንኩን ከውጭ እና ከሃገር ውስጥ ባለሃብቶች እንዲሁም ከኮርፖሬሽኑ ጋር በጋራ በማስተሳሰር ረገድ ጉልህ ሚና መጫወቱንም ዋና ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

በአጠቃላይ ይህ ስምምነት ተዋዋይ ወገኖች የጋራ ጥቅም በሚሰጡ ጉዳዮች ላይ ተባብረው ለመስራት የተስማሙ ሲሆን፣ ይህም በሃገራችን እየተስተዋለ ያለውን የኢኮኖሚ መዋዠቅ እንደሚቀርፍ ታምኖበታል።

በዚሁ ጉዳይ ላይ በአሁኑ ሰዓት ጋዜጣዊ መግለጫ እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን
ግንቦት 22 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *