በወረራ ተይዞ የነበረ 37 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ወደ መሬት ባንክ መግባቱ ተነገረ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተሰራው ስራ በወረራ ተይዘው የነበሩ መሬቶች እየተወረሱ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

በከተማ ደረጃ ከጸጥታ አካላት ጋር በተያያዘ በተሰራው የማጥራት ስራ፣ በህገ-ወጥ መንገድ ተይዞ የነበረን 37 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ወደ መሬት ባንክ እንደሚመለስ ተደርጋል ነው የተባለው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ማሾ ኦላላ፣ የህዝብ እና የሃገር ሃብት የሆነውን መሬት ላልተገባ እና በህገወጥ መንገድ ያስተላለፉ አመራሮች ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተናግረዋል፡፡

ይህ እርምጃ እየተወሰደ ቢገኝም አሁንም መሬትን በህገወጥ መንገድ የሚሰጡ አመራሮች እና ሃፊዎች መኖራቸውን ነው የተናገሩት፡፡
በመሬት ወረራ ተሳትፈው የተገኙ ደላሎች እና ዜጎችም ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ብለዋል፡፡

የመሬት ወረራ እና ዝርፊያ መነሻው በሶስት ነገር ነው ያሉት አቶ ማሾ አንደኛው በአርሶአደሩ ስም የሚነግዱ ሰዎች ሲሆኑ ሁሉተኛው በመልካም አስተዳደር ምክንያት የሚፈጸም ነው፡፡

ሶስተኛው ደግሞ በጥቃቅን እና የስራ እድል ፈጠራ ተመስርቶ የሚፈጸም የመሬት ወረራ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በነዚህ ምክንያቶች ዜጎች ከደላሎች እና ከአመራሮች ጋር በመቀናጀት የመሬት ወረራ እንደሚፈጽሙ ነው የተናገሩት፡፡

በአሁኑ ሰአት ከመሬት ወረራ ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ አቤቶታዎች እና ቅሬታዎች መቀነሳቸውንም አቶ ማሾ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.