የቻይናዉ ፕሬዝዳንት የደህንነት ኃላፊዎቻቸዉ ለማይቀረዉ ትግል እራሳቸዉን እንዲያዘጋጁ አዘዙ፡፡

ፕሬዝዳንት ሺ ጂፒንግ በሀገር ቤትም በዉጭም ጫናዉ እየበረታ በመሆኑ ለደህንነት ኃላፊዎቻቸዉ እጅግ ለከፋዉ ትግል ተዘጋጁ ሲሉ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

ቻይና አሁን ላይ ከፍተኛ የደህንነት፤የኢኮኖሚና የፖለቲካ ጫና ገጥሟታል ያሉት ፕሬዝዳንቱ ፤ይህንን ለመታገል የደህንነትና የወታደራዊ ሃይላችንን ማዘመን አለብን ነዉ ያሉት፡፡

ሀገሪቱ የገጠማትን የደህንነት ስጋት ለመመከትና ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ፈጥኖ ለመረዳት የሚያስችል ሥራ የደህንነት ቢሯቸዉ እንዲሰራ ማዘዛቸዉ ተሰምቷል፡፡

ቤጂንግ ከየብስ እስከ ባህርና ህዋ ድረስ ባሉ ግዛቶቿ የሚቃጡ ጥቃቶችን መመከት የሚያስችል ስራዎችን እንደምትሰራም ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም እያደገ የመጣዉን የሳይበር ጥቃት ለመግታት የደህንነት ኃላፊዎቻቸዉ በንቃት እንዲከታተሉ ማሳሰባቸዉን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል፡፡

ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ቻይና ከምዕራቡ አለም ጋር ከፍተኛ ዉጥረት ዉስጥ መግበቷ ይታወሳል፡፡

በአባቱ መረቀ

ግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *