ራሚስ ባንክ የኢትዮጵያን የባንክ ኢንዱስሪ ሊቀላቀል ነው።

ላለፉት ሁለት አመታት የአክሲዮን ሽያጭ ሲያደርግ የቆየው ባንኩ ከመጪው እሁድ ጀምሮ በይፋ ስራ ሊጀምር መሆኑን በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ባንኩ ከ 8 ሺህ በላይ የአክሲዮን አባላት ያሉት ሲሆን በ 2 ቢሊየን ብር ካፒታል ወደ ስራ ሊገባ መሆኑን ገልጿል።

የባንኩ የተከፈለ ካፒታል ከ636 ሚሊየን ብር በላይ መሆኑን የራሚስ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አሊ አህመድ ተናግረዋል።

ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመው ራሚስ ባንክ፣ ትኩረት ያልተሰጣቸው ዘርፎችን ለመደገፍ አላማው አድርጎ እንደሚሰራ የባንኩ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል።
የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽ ያልሆነባቸው የሃገሪቱ አካባቢዎችን ለመድረስ በትኩረት ይሰራልም ብለዋል።

ባንኩ በሃገሪቱ የሚስተዋለውን የሃብት አለመመጣጠን ችግር ለመፍታት የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀቱንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ባንኩ የዋስትና ማስያዣ የሌላቸውን ሰዎች እና የመንቀሳቀሻ ካፒታል እጥረት ያለባቸውን ሰዎች ከንግድ ስራ ጋር በሽርክና በማገናኝት ህልማቸውን እውን እንዲያደርጉ እገዛ አደርጋለሁ ብሏል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.