የሱዳን ተኩስ አቁም ስምምነት መጣሱ እንዳሳሰባት አሜሪካ ገለጸች።

የአሜሪካ መንግስት የሱዳን ተፋላሚ ሀይሎች የተኩስ አቁሙን መጣሳቸዉ እንዳሳሰበዉ በመግለፅ የሰብዓዊ ርዳታ ተደራሽነት ለማመቻቸት ያላቸዉ ቁርጠኝነት ጥርጣሬ ዉስጥ መግባቱን አስታውቋል።

የአሜሪካ መንግስት የዉጭ ጉዳይ ቢሮ እንዳስታወቀው ከሆነ ” እንደ አንድ የድርድሩ አስተባባሪ እየተጣሱ ያሉት የተኩስ አቁም ስምምነቶች የሱዳንን ህዝብ ወክለዉ የወሰዱትን ግዴታ ተረክበዉ እርምጃ ለመዉሰድ ዝግጁ መሆናቸውን ጥያቄ ዉስጥ የሚከት ነዉ ሲል ወቅሷል”።

በዋና ከተማዋ ካርቱም በትላንትናዉ ዕለት ግጭቱ ተባብሷ መቀጠሉን የአይን ዕማኞች ገልጸዋል።

በተለይም በዋና ከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ካርቱም፣ባህሪ እና ኦምዱርማን ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉ ተገልፃል።

እነዚህ አካባቢዎች በናይል ወንዝ ዙሪያ የሚገኙና በአፍሪካ በርካታ የህዝብ ቁጥር ካለባቸዉ ከተሞች መካከል ናቸው።

በአቤል ደጀኔ

ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.