በጨረታ ወቅት የሚፈጠሩ ብልሹ አሰራሮችን የሚከላከል የዲጅታል ሲስተም ወደ ስራ ሊገባ ነው፡፡

ኦክሽን ኢትዮጵያ አክስዮን ማህበር ዘመናዊ የጨረታ ስርዓትን ለማሳለጥ የሚያስችል እና ብልሹ አሰራርን ያስቀራል የተባለለትን የዲጂታል አሰራርን ይፋ አድርጓል።

“እኮሽን ኢትዮጵያ” የመንግስትም ሆኑ የግል ተቋማት በቀላሉ መጠቀም የሚችሉት ሲስተም እንደሆነ የአክሲዮን ማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሴፍ አንኩ ተናግረዋል።
ተጫራቾች በእጅ በሚይዟቸው ስልኮቻቸው ካሉበት ሆነው መጫረት እንዲችሉ የሚረዳ ነው ያሉም ሲሆን፣አሰልቺ የሆነ የጨረታ ሂደትን እንደሚያስቀር ገልጸዋል።

በጨረታ ሂደቱ ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት እንዳይፈጠሩ የተዘረጋው ሲስተም በራሱ ይከለክላል ብለዋል።
የጨረታውን አሸናፊ በፍትሃዊነት እና በቀላሉ መለየት የሚችለው ሲስተሙ፣ የኢንተርኔት አቅማቸው ደካማ በሆኑባቸው አከባቢዎች የሚገኙ አካላትም መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።

ተጫራቾች የሚከወኑ ጨረታዎችን የጨረታ አይነቶችን እና ዝርዝሮች መመልከት የሚችሉበት ሲስተሙ፣ ከባንኮች ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ለጨረታው አስፈላጊ የሆኑ ክፍያዎች በቀላሉ እንዲፈፀሙ እንዲሁም ከጨረታውም በኃላ ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል ተብሏል።

በሚቀጥለው ወር ተግባራዊ ይሆናል የተባለው ቴክኖሎጂ፣ የኢንሹራንስ ድርጅቶች፣የመንግስት ተቋማት፣የውጭ ተቋማት እና የተለያዩ የቢዝነስ ድርጅቶች ከሙስና በፀዳ መልኩ መሳተፍ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን

ሰኔ 01 ቀን ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.