ኢትዮጵያ በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት እንደምታደንቅ አሜሪካ አሳወቀች፡፡

የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኩንን በሳውዲ ሪያድ እየተካሄደ ባለው አይ ኤስ አይ ኤስ የሽብር ቡድንን ለመዋጋት በተቋቋመው ዓለም አቀፍ ጥምረት የሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ ከተገኙት የአሜሪካው አቻቸው አንቶኒ ብሊንከን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በወይይታቸውም በህዳር ወር ከተደረሰው ስምምነት ጋር ተያይዞ በሰሜን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የተመዘገበውን እድገት አሜሪካ እንደምታደንቅ አብራርተዋል፡፡

በትግራይ ክልል ከሰብአዊ ዕርዳታ ጋር በተያያዘ አጋጠመ የተባለውን ዝርፊያም የኢትዮጵያ መንግስት ሙሉ ምርመራ ለማካሄድ እና ተጠያቂነትን ለማስፈን በጋራ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት በደስታ እንቀበለዋለን ብለዋል አንቶኒ ብሊንከን፡፡

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን እና አንቶኒ ብሊንከን ምዕራብ ትግራይን ጨምሮ የሰብአዊ መብት አያያዝን በተመለከተም ተወያይተዋል።

ግልጽ እና ሁሉን አቀፍ የሽግግር የፍትህ ሂደትን ማራመድ፤ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችን መፍታትንም ያካተተ ውይይት ማደረጋቸውን የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ተናግረዋል።

በያይኔአበባ ሻምበል

ሰኔ 01 ቀን ቀን 2015 ዓ.ም
ፎቶ—ፋይል

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *