“የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ንቁ ተሳትፎ ዘላቂ ለሆነ ሰላም፣ ሰብዓዊ መብትና መልካም አስተዳደር” በሚል መሪ ሀሳብ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚካሄደው የሲቪል ማህበራት ድርጅት ሳምንት ኤግዚቢሽን እና ባዛር ትናንት በጊዮን ሆቴል የመክፈቻ ስነ-ስረዓቱ ተካሂዷል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከየሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ጋር በጋራ ባዘጋጀው በዚህ ሁነት፤ የመወያያ ፅሁፎች ቀርበው የፖናል ውይይቶች እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።
የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች የሰላም እና ድህረ ግጭት የሰላም ግንባታ፣ የሽግግር ፍትህ፣ የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ፣ስነ-ፆታ እና መሰል ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ፅሁፎች እንደሚቀርቡ ተመላክቷል።
በእሌኒ ግዛቸው
ሰኔ 01 ቀን ቀን 2015 ዓ.ም











