በወልቂጤ ከተማ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የትራንስፖርት ስምሪት አሰጣጥ ስርአት (ኢ_ቲኬቲንግ) ተጀምሯል።

ህብረተሰቡ ከታሪፍ በላይ እንዳይከፍል፣ ተሳፋሪን ከእንግልት የሚታደግ ፣ትርፍ እንዳይጫን የሚያደርግ እና ዘመናዊ መናኸርያ እንዲፈጠር የጎላ ሚና ይኖረዋል የተባለለት አዲስ ቴክኖሎጂ መጀመሩ ታውቋል።

ቴክኖሎጂው ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት ከመስጠቱ በተጨማሪ ሙሉ የመኪና መረጃዎችን የሚያሳውቅ ነው ተብሏል።

በወልቂጤ ከተማ የተጀመረው ይህ ቴክኖሎጂ(ኢ_ቲኬቲንግ) በደቡብ ክልል የመጀመርያው ነው።

የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ሲስተም አስተባባሪ አቶ ቢኒያም ፈቃዱ፣ ቴክኖሎጂው ለህብረተሰቡ በታሪፉ ልክ ቲኬት መቁረጥ፣ለመኪናዎች መውጫ መስጠትና ቅደም ተከተል የማሰያዝ ስራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ቴክኖሎጂውን በተመለከተ ከአሽከርካሪዎች ማህበር፣ ከትራፊክና ከፖሊስ መዋቅሮች ጋር ውይይት ተደርጎ መግባባት ላይ ተደርሷል መባሉን ሄኖክ ወ/ገብርኤል ዘግቧል፡፡

ሰኔ 05 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.