የቀድሞዉ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር አሜሪካ እንድታሰር ዶልታብኛለች አሉ፡፡

የቀድሞዉ የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካህን ከሩሲያ ጋር በነበረኝ ግንኙነት ምክንያት አሜሪካ እንዳሳሰረቻቸው ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈዉ ወር በሙስና ጉዳይ ተጠርጥረዉ ለእስር ተዳርገው ነበር፡፡ ከእስራት ባሻገር ከስልጣን ለመዉረዳቸዉም አሜሪካ ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖ ተጠቅማለች ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ከኒዉስ ዊክ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ በጥር 2022 ሩሲያ ዩክሬን ላይ ጦርነት ባወጀችበት በዛኑ ዕለት ሞስኮ ገብተዉ እንደነበር ያነሱት ኢምራን ካህን፣ በሰዓቱ የሄዱበትን የንግድ ስምምነት ላለማጣት ሲሉ የሩሲያን ተግባር መኮነን እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን አሜሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኩል የሩሲያን ተግባር እንድናወግዝ የጠየቀችን ቢሆንም፣ ከሩሲያ ጋር በገባነዉ የንግድ ስምምነት መሰረት በዝቅተኛ ዋጋ ነዳጅ እና ስንዴ ወደ አገራችን ለማስገባት በመስማማታችን ያንን ማድረግ አልቻልንም ነበር ነዉ ያሉት፡፡

“አሜሪካ እንዳለችዉ ሩሲያን ብናወግዝ በዜጎቻችን ላይ ሊኖረዉ የሚችለዉን ተጽዕኖ በማሰብ ያንን ማድረግ አልቻልንም፣በዚህም አሜሪካ በሴራ ከስልጣን እንድወርድ እና እንድታሰር አድርጋለች” ሲሉ መናገራቸዉን አርቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ሰኔ 05 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.