መግለጫው እኔን አይወክለኝም….ኢህአፓ፤

32 የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሳተፉበትና እራሱን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ግዚያዊ ኮሚቴ በሚል የጠራዉ አካል ያወጣዉ መግለጫ ኢህአፓን እንደማይወክል ፓርቲዉ ገልፆል።

ፓርቲዉ ባልዋልኩበት የፓርቲዬ ስም መጠራቱ በእጅጉ አስዝኖኛል ሲል ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

የኢህአፓ ተቀዳሚ ፕሬዚዳንት እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የአቅም ግንባታ ዋና ሰብሳቢ የሆኑት መምህር አብርሃም ሀይማኖት ከጣብያቸን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ በዋና ስራ አስፈፃሚዉ በሰኔ 2/10/2015 ዓ.መ የወጣዉ መግለጫ በተለይም በሸገር ከተማ እየተከናወነ ያለዉን የቤት እና ቤተ ዕምነት ፈረሳ፣በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለዉን በደል እንዲሁም የኢኮኖሚዉን የዋጋ ንረት በተመለከተ ያወጣዉን መግለጫ ፓርቲያችን የደገፈ ቢሆንም እራሱን ግዜያዊ ኮሚቴ ብሎ በ32 ፓሪቲዎች ተዋቅሬያለዉ ያለዉ አካል ፓርቲያችንን የዋና ስራ አስፈፃሚዉን መግለጫ ተቃዉሟል ተብሎ ስማችን መነሳቱ በእጁጉ ከማሳዘኑም በላይ ትክክልም አይደለም ብለዋል።

ኢህአፓ በትላንትናው ዕለት 07/10/2015 ዓ.ም በጊዜያዉ ኮሚቴ የተሰጠዉ መግለጫ እንደማይወክለዉም አስታዉቋል።

ኢህአፓ አሁንም ቢሆን በዋና ስራ አስፈፃሚዉ የተሰጠዉን መግለጫ እንደሚደግፍ እና በተለይም በሸገር ከተማ እየደረሰ ያለዉ የቤት እና ቤተ ዕምነት ፈረሳ በአስቸኳይ እንዲቆም፣ ሀይማኖቶች ላይ እየተደረገ ያለዉ በደል፣ፓሪቲዎች ላይ እየተደረ ያለዉን ጫና እንዲሁም የኢኮኖሚዉ የዋጋ ንረት በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጠዉ አቋሙ መሆኑን ፓርቲዉ አስታውቋል።

ፓርቲዉ ይህ አቋሙ በቅርቡ ዉህደት የፈፀማቸዉ እናት ፓርቲ እና የመኢአድ መሆኑንም ይታወቅልኝ ብሏል።

በአቤል ደጀኔ

ሰኔ 08 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.