ሩሲያ በየአመቱ ለአንድ መቶ ኢትዮያውያን ነፃ የትምህርት ዕድል እንደምትሰጥ አስታወቀች፡፡

የሀገሪቱ ኢምባሲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው፣ ሩሲያ በየአመቱ ለአንድ መቶ ኢትዮጵያውያን ነፃ የትምህርት ዕድል ትሰጣለች ብሏል።

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ይቭገኒ ትረኪን ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የሩሲያ መንግስት በትምህርት ዘርፍ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ሞስኮ በየአመቱ ለዘጠኝ ኢትዮጵያውያን ነፃ የትምህርት ዕድል ትሰጥ እንደነበር አስታውሰው፣በቀጣይ ለአንድ መቶ ኢትዮጵያውያን ዕድሉ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

ሀገሪቱ ከሶቭየት ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያን በትምህርት ዘርፍ ስትደግፍ መቆየቷንም አስታውሰዋል።

የሁለቱን ሀገራት ግንኘነት በትምህርቱ ዘርፍ ከፍ ለማድረግ እንደሚሰሩም አምባሳደሩ ተናግረዋል።

ከሰሞኑም የሩሲያ ኢምባሲና ባሕር ዳር ዩንቨርስቲ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት አድርገዋል።

በአባቱ መረቀ

ሰኔ 08 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.