“ንግድዎን በመቅረዝ ላይ ያኑሩ” ዓለም አቀፍ አውደ-ርዕይ እና ኮንፈረንስ፤

“ንግድዎን በመቅረዝ ላይ ያኑሩ” በሚል መሪ ቃል የፈርኒቸር፤የቤት ውበት እና የግንባታ አጨራረስ ምርቶች፣አገልግሎቶች እና ቴክኖሎጂ ዓለምአቀፋዊ አውደ-ርዕይ እና ኮንፈረንስ ዛሬ ተጀምሯል።

ዛሬን ጨምሮ ለአራት ቀናት በሚሊኒየም አዳራሽ የሚደረገው አራተኛው ዓለምአቀፋ አውደ-ርዕይ እና ኮንፈረንስ፣ ዘላቂ የንግድ ትስስርን ለመፍጠርና እድገትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ተብሏል።

በፕራና ኢቨንትስ እና በአፍሪካን ትረስትድ በጋራ የተዘጋጀው አወደ-ርዕይ ተሳታፊዎችን ሁሉንም በየዘርፉ ተጠቃሚ በማድረግ የተሻለ የንግድ ስኬትን ይፈጥራል ተብሏል፡፡

“Fintex”ን ለማጠናከር ከአሜሪካ፣ከደቡብ አፍሪካ ፣ከስዊድን እና ከተባበሩት አረብ ኢምሬት ሃገራት በጋራ እየሰራ መሆኑንም ገልጿል።

ድርጅቱ ከነዚህ ሃገራት ጋር በአካል እና በበይነ መረብ በሚያደርገው የውይይት መድረክ፣የውጭ ሃገር የፕሮጀክት ፋይናንስ የሚኝበትን እና የጋራ ኢንቨስትመንትን ማሳደግ የሚቻልበትን እድል እያሰፋ ነው ብሏል።

ከኬንያ ፣ከፖላንድ እና ከኔዘርላንድ በተጋበዙ አለምአቀፍ ባለሞያዎች የገበያ ተደራሽነትን ለማሳለጥ ፣ምርትን ፣አገልግሎትን እና የኩባንያ ማንነትን አጉልቶ ለማውጣት እየተሰራ እንደሚገኝም በመርሃ-ግብሩ ላይ ሰምተናል፡፡

ይህም በሃገራችን የሚገኙ በዘርፉ ያሉ ድርጅቶች በአለማቀፍ የንግድ መድረክ ላይ ተወዳዳሪነታቸውን እንደሚያሳድግላቸው የአፍሪካ ትረስትድ ፖርትነር ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ አክሊሉ በለጠ ተናግረዋል።

በአውደ-ርዕዩ በርካታ የሃገር ውስጥ አምራች ኩባንያዎች የሚሳተፉ ሲሆን፣ከ4000 በላይ የንግዱ ማህበረሰብ አባላትና ጎብኚዎች እንደሚስተናገዱ ይጠበቃል ተብሏል።

በመሳይ ገ/መድህን
ሰኔ 08 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.