ጋዜጠኛ ህይወት ታደሰ ከ 50 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል ድጋፍ አደረገች፡፡

ነዋሪነቷን በሰሜን አሜሪካ ያደረገችው ጋዜጠኛ ህይወት ታደሰ፣ ከ 50 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ በዛሬው እለት ለኢትዮጵያ የልብ ህሙሟን ህፃናት መርጃ መዕከል ድጋፍ አድርጋለች።

ጋዜጠኛ ህይወት ታደስ ላለፉት አራት አመታት የልደት ቀኗን ምክንያት በማረግ “ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ” በሚል መሪ ቃል ለማዕከሉ የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ በማረግ ድጋፍ ስታረግ መቆየቷ ነው የተገለጸው።

ጋዜጠኛ ህይወት ታደሰ የጀመረችውን በጎ አድራጎት ለማጠናከር “ላይፍ ኦፍ አፍሪካ” የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በአሜሪካ ያቋቋመች ሲሆን፣ በዘንድሮው የልደት ቀኗም ከ 50 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጋለች።

ለማዕከሉ እጅግ ጠቃሚ የሆኑና በቀላሉ የማይገኙ የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ እንዳደረገች የተነገረላት ጋዜጠኛ ህይወት ታደሰ፣ “በተለይም በርካታ ተከታይ ያለን ታዋቂ ሰዎች ልባቸው ተሰብሮ ወረፋ እየተጠባበቁ ላሉ ምስኪን ህፃናት ህይወታቸው እንዳያልፍ በማህበራዊ ሚዲያ ልንደርስለቸው ይገባል” ስትል ተናግራለች።

የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል ላለፉት 30 አመታት፤ ከሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የልብ ህሙማን ታካሚዎችን በመላክ የልብ ቀድዶ ህክምና እና የደም ስር መጥበብ ሲያረግ የቀየ ሲሆን፣ 3000 ለሚሆኑ ታካሚዎች ያለምንም ክፍያ ከተለያዩ ልበ ቀና ከሆኑ ግለሰቦች እና ሀገር በቀል እንዳሁም ከሀገር ወጭ በሚደረግ እርዳታ ማከናወኑም ተመላክቷል።

በአሁኑ ሰአት ከ 7 ሺህ በላይ ቀዶ ጥገና የሚጠባበቁ ህፃናትና ታዳጊዎች መኖራቸው የተገለፀ ሲሆን፣ በአለማችን ብሎም በሀገራችን በተከሰተው የcovid 19 ወረርሽኝ ምክንያት ከዚህ ቀደም ይላኩ የነበሩ የተለያዩ የህክምና መሳሪያዎችን አሁን ላይ በቀላሉ ማግኘት እየተቻለ እንዳልሆነም ተነግሯል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው
ሰኔ 08 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.