ፊፋ ጨዋታ እየተካሄደ በተጨዋቾች ላይ የዘረኝነት ጥቃት የሚሰነዘር ከሆነ ጨዋታው እንዲቋረጥ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በእግር ኳስ ሜዳ ላይ ለሚፈፀም የዘርኝነት ጥቃት ምንም ዓይነት ትዕግስት እንደሌለው ገልፀዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ እንደገለፁት በጨዋታ መሀል የዘርኝነት ጥቃት የሚሰነዘር ከሆነ ዳኞች ጨዋታውን ወድያውኑ እንደሚያቋርጡት አስታውቀዋል፡፡

ጂያኒ ኢንፋንቲኖ የሪያል ማድሪዱን ተጨዋች ቪኒሲየስ ጁኒየርን አግኝተው ባለፈው ወር በጨዋታ ላይ ስላጋጠመው የዘረኝነት ጥቃት መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡

ዘርኝነትን በጋራ መዋጋት የሁሉም ሀላፊነት መሆኑን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ፣ የዘርኝነት ጥቃት የሚሰነዝሩ ወንጀለኞችን የመቆጣጠሩን ሀላፊነት የፊፋ ባለስልጣናት ሊወስዱ ይገባል ብለዋል፡፡

ዘርኝነት ካለ እግር ኳስ ጨዋታ የለም ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ይህ ሲሆን ጨዋታዎች ሊቆሙ እንደሚችሉ ገልፀዋል፤ ዋና ሀላፊነቱንም ዳኞች ይወስዳሉ እንዲህ ያለ ክስተት ሲያጋጥማቸው የማስቆም ሀላፊነት አላቸው ብለዋል፡፡

ይህ ደግሞ በሁሉ የውድድር ዓይነት ሊተገበር እንደሚችልም ጂያኒ ኢንፋንቲኖ መናገራቸውን የዘገበው አልጀዚራ ነው፡፡

በአቤል ደጀኔ

ሰኔ 09 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.