የሩሲያ ጦር በተለያዩ የዩክሬን ከተሞች መጠነ ሰፊ የአየር ላይ ጥቃት መክፈቱ ተሰምቷል፡፡
የአየር ኃይሉ የዩክሬን ዋና ከተመዋን ኬይቭን ጨምሮ መጠነ ሰፊ ጥቃት እየፈጸመ እንደሚገኝ የዩክሬን ባለስልጣናት አስታዉቀዋል፡፡
ሞስኮ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ አቅጣጫ ባሉ የዩክሬን ከተሞች ላይ የድሮንና የሚሳኤል ጥቃት ወስዳለች ነዉ የተባለዉ፡፡
በእነዚህ ግዛቶች ዉስጥ የሚገኙ ከተሞችም በጥቃቱ የኃይል መስመራቸዉ በመቋረጡ በጨለማ ተዉጠዋል ተብሏል፡፡
ዩክሬን የመልሶ ማጥቃት ዘመቻዉን ከጀመረች በኋላ በሩሲያ አየር ሃይል ክፉኛ እየተደበደበች ስለመሆኗም አልጄዚራ ዘግቧል፡፡
በመልሶ ማጥቃቱ ዩክሬን 8 ትናንሽ ከተሞችን ከሩሲያ ጦር መረከቧን ብታሳዉቅም አሁን ላይ ከሞሰኮ አየር ኃይል ከባድ ጥቃት እያስተናገደች ነዉ፡፡
የሩሲያ የደህንነት ሰዎችም የዩክሬን መልሶ ማጥቃት ዘመቻ ዋጋቢስና የትም የማያደርስ ነዉ እያሉ ነዉ ሲል አርቲ አስነብቧል፡፡
በአባቱ መረቀ
ሰኔ 13 ቀን 2015 ዓ.ም











