ከጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ላለፉት አምስት ወራት እስር ላይ የነበሩ ዜጎች ከእስር መለቀቃቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከታራሚ ቤተሰቦች አረጋግጧል፡፡
ዜጎቹ ለእስር ተዳርገው የነበሩት ሃሰተኛ መረጃ አሰራጭታችኋል፣ብጥብጥ እንዲቀሰቀስ አድርጋቹሃለ በሚል ነበር፡፡
ከታሳሪዎቹ መካከልም የህግ ባለሙያዎች፣ በዞኑ በተለያየ የመንግስት መስሪያ ቤት በከፍተኛ አመራርነት ሲያገለግሉ የነበሩ አመራሮች እና “ለጉራጌ ህዝብ መብት እንታገላለን” የሚሉ ዜጎች እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡
በወልቂጤ ከተማ ተይዘው በደቡብ ክልል እስር ላይ የነበሩ 4 “የጉራጌ የመብት ተሟጋቾች ነን” ያሉ ሰዎችም በ50ሺህ ብር የገንዘብ ዋስ ከእስር የተለቀቁ ሲሆን ጉዳያቸውን ወልቂጤ ሆነው እንዲከታተሉ የደብብ ክልል ፍርድ ቤት ትዛዝ መስጠቱም ታውቋል፡፡
በተጨማሪም 16 የሚጠጉ የዞኑ ተወላጆች ያለ ምንም ዋስትና ከእስር የተለቀቁ ሲሆን፣ ጉዳያቸው ከዚህ በኃላ በወልቂጤ ከተማ ፍርድ ቤት እንዲታይ ተደርጓል ተብሏል፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 14 ቀን 2015 ዓ.ም











