በአውሮፓ ግዙፉ የውሃ ማጠራቀሚያ ግድብ የመድረቅ አደጋ ተጋርጦበታል ተባለ፡፡

በደቡባዊ ዩክሬን የሚገኝውና በአውሮፓ በግዙፍነቱ ቀዳሚ መሆኑ የሚነገረው የካክሆቫክ ግድብ፣ በሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ጉዳት እንደደረሰበት ቀደም ሲል ተገልጾ ነበር፡፡

የቢቢሲ ከሳተላይት ምስል ያገኘሁት ነው ብሎ ባሰራጨው ዘገባ በውሃ ማጠራቀሚያ ግድቡ ውስጥ የነበረው ውሃ መጠኑ በእጅጉ እየቀነሰና የመድረቅ ጫፍ ላይ መሆኑን ያሳያል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዳለው፣ በዚህ ምክንያት እስከ 700 ሺህ ያህል ዜጎች ንጹህ የመጠጥ ውሃ እንዳያገኙ ያደርጋል፣በተለይም በሩስያ በተያዙ አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎች የዚህ ተጎጂ ናቸው ብሏል፡፡

ባለሙያዎች ደግሞ የውሃ ማጠራቀሚያው ሙሉ በሙሉ የሚደርቅ ከሆነ በምግብ ምርት ላይም የጎላ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል እያሉ ነው፡፡

የካክሆቫክ ግድብ ጥቃት ከደረሰበት በኋላ የሳተላይት ምስሎች በውሃ ማጠራቀሚያው ውስጥ ያለው የውሃ መጠን እና ከገባር ወንዞች የሚገባው የውሃ መጠን በከፍተኛ ደረጃ መውረዱን ያሳያሉ።
ይህ የውሃ ማጠራቀሚያ ለደቡባዊ ዩክሬን ሰፋፊ የእርሻ መሬቶች ለመስኖ አገልግሎት እንዲውሉ ከፍተኛ ሚና ነበረው፡፡

5ሺህ 840 ኪሎሜትር ወይም 584ሺህ ሄክታር መሬት ይሸፍን የነበረው የካክ ሆቫክ ግድብ በፈረንጆቹ 1956 እንደተገነባ መረጃዎች ያለመክታሉ፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 15 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.