የኬሚካል ውጤቶች የተቀላቀለበት 26 ኩንታል ሊፈጭ የተዘጋጀ በርበሬ ተያዘ፡፡

እንዲሁም 8 ኩንታል ባዕድ ነገሮች የተቀላቀለበት የተፈጨ በርበሬ ከ 9 ኩንታል የኬሚካል ውጤቶች ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉ ተጠቁሟል።

በጉራጌ ዞን በዳርጌ ከተማ በርበሬ በማስመሰል ወደ ገበያ ሊወጡ የነበሩ ግብዓቶች ከአዘጋጆቹ ጭምር በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ነው የተባለው።

የወረዳው ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሽመልስ አይተንፍሱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ተጠርጣሪዎቹ የበርበሬ ምርት እንዲመስል ጎጂ ኬሚካሎችንና ባዕድ ነገሮችን በማዘጋጀት ወደ ገበያ ለማውጣት አስበው ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልጸው፣ ከህብረተሰቡ በተገኘ ጥቆማና የፍተሻ ስራ ሊያዝ መቻሉን ጨምረው ገልፀዋል።

ግብዓቶቹ ወደ ገበያ ለግብይት ቢቀርቡ ኖሮ የሸማቹን ማህበረሰብ ጤና በከፍተኛ ደረጃ የሚጎዱ እንደነበሩ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ጊዜ ያለፈባቸውና የተከለከሉ የገበታ ጨው፣ የለስላሳና የዘይት ምርቶችንም በተደረገ የኢንስፔክሽን ስራ መያዛቸውም ተመላክቷል።

በድርጊቱ የተጠረጠሩ እና ባዕድ ነገሮችን ሲያዘጋጁ የተያዙ አካላት በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል ተብሏል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሰኔ 15 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.