4ኛ ዙር የታላቁ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ተባለ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ኢትዮጵያ ዘንድሮ ሕዳሴ ግድብን ለአራተኛ ጊዜ በውሃ ለመሙላት ዝግጅት ላይ መኾኗን ተናግረዋል፡፡

አቶ ደመቀ ይህን የተናገሩት በድንበር ዘለል ወንዞች አጠቃቀም ዙሪያ ትናንት በአዲስ አበባ በመከረው የቀጠናው ከፍተኛ የሚንስትሮች ስብሰባ ላይ ነው፡፡

በዚሁ መድረክ ላይም “ሕዳሴ ግድብ የአገራት የጋራ ሃብት የኾነውን ወንዝ ለብቻቸው መጠቀም የሚፈልጉ ኃይሎችን አሉታዊ ትርክት በመቋቋም፣ ወደ መጠናቀቂያው ምዕራፍ እየተቃረበ” መኾኑን ገልጸዋል፡፡

“ሕዳሴ ግድብ የፍትሃዊና ምክንያታዊ ውሃ አጠቃቀም ተምሳሌት ነውም ብለዋል፡፡
በስብሰባው ከኢትዮጵያ በተጨማሪ፣ ኡጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ታንዛኒያ እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ ታድመው ነበር።(ዋዜማ)

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 16 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.