ሩሲያ ዉስጣዊ የደህንነት ስጋት እንደተደቀነባት አስታወቀች፡፡

ሩሲያ ዉስጣዊ የደህንነት ስጋት እንደተደቀነባት አስታወቀች፡፡
የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚካኤል ሚሹስቲን እንዳስተወቁት ከዋግነር የአመፅ ሙከራ በኋላ የደህንነት ስጋት ገጥሞናል ብለዋል፡፡

ከድርጊቱ ማግስት የሩሲያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚካኤል ሚሹስቲን ለካቢኒያቸዉ በሰጡት መግለጫ ሀገረ ሩሲያ ከባድ የፖለቲካና የደህንት አደጋ ዉስጥ ወድቃለች ሲሉ በግልፅ ተናግረዋል፡፡

ከዉጭ ብቻም ሳይሆን በሀገረ ቤት አደገኛ የሆነ የደህነት ስጋት መኖሩን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒሰትሩ የጸጥታ አካላት በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ትዕዛዝ ሰጥዋል፡፡
የምእራቡ አለም የሚፈርኩት ሴራ የክሪሚሊን አስተዳደር በሃይል ለማነድ እየሰተራ ነዉ ሲሉም በግልጽ አስታዉቀዋል፡፡

እናም ሁሉም ሩሲያዊ ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስተዳሰደር ጎን በመቆም የተቃጣብንን ሴራና የደህንት ስጋት በጋራ እንመክት ሲሉ ጥሪያቸዉን አቅርበዋል፡፡

ይህ ደግሞ የፑቲን አስተዳደር በክሬን ጦርነት ምክንያት አደጋ ላይ ወድቋል በሚል በምእራባዉያኑ እንዲተች አስገድዶታል፡፡

ከቦልሹቪስኩም ከሴዛሩም አበዮት ይህ የተለየ አመፅ ነዉ፡፡
ይህ ከዳቦዉም ከመሬቱም ከሰላሙም መፈክር በእጅጉን ይለያል፡፡

በርግጥ 1917ቱን አብዮት ያቀጣጠለዉ የመጀመሪያዉ የአለም ጦርነት ምድረ አዉሮፓን በማዉደሙ በሰራተኛ መደብ ላይ ብቻም ሳይሆን በጭሰኛዉና በተማራዉ ሃይል ላይ ቁጣን በመቀስቀሱ የሞስኮ በጦርነቱ መሳተፈፍ እንደ ምክንያት ይነሳል፡፡

ሰሞኑን በሞስኮ የተሞከረዉ አመጽና የመንግስት የግልበጣ ሙከራ መሰረቱ የዬክሬኑ ጦርነት ነዉ፡፡

ነገርየዉን ለየት የሚያደረገዉ ግን አመጹ ህዝባዊ ሳይሆን በቅጥረኛ ወታደሮች ቡድን የተመራ መሆኑ ነዉ፡፡

ክህደት ብለዉ ፕሬዝዳንት ፑቲን የጠሩት የፕሪጎዢን አመፅ ያሰበዉን ሳያሳካ መቆጣጠር ቢቻልም የክሪሚሊን አለቆች ግን እንቀልፍ እንዳይተኙ አድርጓቸዋል፡፡

የፑቲን አስተዳደርም በሀገሪቱ አስከፊ አብዮት እንዳይነሳ ጥብቅ ጥንቃቄ እንዲደረግ የጦር አመራሮችን ማዘዙ እየተነገረ ነዉ፡፡

የ1917ቱ የሩሲያ አብዮት የሴዛርን ስረዉ መንግስት አሽቀንጥሮ በመጣል የቦልሼቪስክ ፓርቲዉ ስልጣኑን እንዲቆጣጠር እድል በመፍጠሩ ለረጅም አመታት ስልጣንን የሙጥኝ ያለዉ አገዛዝ ተወግዷል፡፡

በኋላ ላይ የሶቪይት ህብረት እንድትመሰረትም ምክንያት መሆኑን ታሪክ ያስረዳል፡፡

ታዲያ በዩክሬን ምድር እየተካሄደ ያለዉ ጦርነት በሩሲያ የጦር አመራሮች ምክንት የ1917ቱ አይነት አብዮት ሊቀስቀስ እንደሚችል ፑቲንን የደረፈረዉና የቅርብ ሰዉ የቭገኒ ፕሪጎዢን ከአንድ ወር በፊት አስጠንቀቆ ነበር፡፡

እናም እንዳሰበዉ ባይሆንም እንደ አለት የጠነከረዉን የፑቲንን አስተዳደር መነቅነቅ ሙከራ በማድረጉ ሞስኮን ስጋት ላይ ጥሏታል፡፡

የሩሲያ ጥላቶችም የፑቲን አስተዳደር ደካማና የተፈረካከሰ ነዉ እንዲሉ እድል ፈጥሮላቸዋል፡፡

በርግጥ ይህን ሙከራ ካደረገ በኋላ የቅጥረኛ ቡድኑ ዘዋሪ የቭገኒ ፕሪጎዢን ባስተላለፈዉ መልእክት እኛ የፑቲንን አስተዳደር ለመገልበጥ ሳይሆን በጦር አመራሩ ኢፍታዊ አሰራር በመኖሩ እሱን ለማሳወቅ ነዉ ማለቱን አልጄዚራና ሲ ኤን ኤን ዘግበዋል፡፡

ይሁን እንጅ የምእራቡ አለም ፖለቲከኞች ብቻም ሳይሆን የፑቲን አስተዳደርም ከፍተኛ የሆነ ችግር እንደገጠመዉ በግልፅ መናገር መጀመሩን ዘገባዉ አስፍሯል፡፡

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ ዋና ፀኃፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ በሰጡት መግለጫ የቅጥረኛ ወታደሩ ዋግነር ከሰሞኑ ሞስኮ ላይ ያደረገዉ የፑቲን አስተዳደር ምን ያህል እንደተንኮታኮተና ደካማ መሆኑ የሚያሳይ ነዉ ብለዋል፡፡

ዋና ፀሃፊዉ ለዩክሬን የምናደርገዉን የጦር መሳሪያ ድጋፍ አጠናክረን በመቀጠል ይህንን አገዛዝ ማዳከማችንን እንቀጥላለን ነዉ ያሉት፡፡

የአዉሮፓ ህብረት የዉጭ ጉዳይ ፖሊሲ ሃላፊዉ ጆሴፍ ቦሬል በበኩላቸዉ የሩሲያ መንግስትና ጦሩ እየተናደ መሆኑን ያሳያል ማለታቸዉን ሲ ኤን ኤን አስነብቧል፡፡

ወደ ሉግዘንበርግ ያቀኑት የጀርመኗ የዉጭ ጉዳይ ነሚኒስትር አናሌና ቤርቦክም ፕሬዝዳንት ፑቲን ገና ምን አይቶ ከፍተኛ መኣት ይመጣበታል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ በርሊን ከዩክሬን ጎን በመቆም የፑቲን አስተዳደርን ወድቀት ታፋጥናለች ነዉ ያሉት፡፡

በሀገር ቤትም በዉጭም ጫና ዉስጥ የወደቁት የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጦራቸዉ በዩክሬኑ አዉደ ዉጊያ ድል እየራቀዉ መሆኑንም የዩከሬን ባለሰልጣናት እያስጣወቁ ነዉ፡፡

የዩክሬን ሰራዊት በደቡባዉ የሀገሪቱ አዉደ ዉጊያ ተጨማሪ ድሎችን እያስመዘገበ ከፑቲን ጦር መንጋጋ ከተሞችን እየመነገገ እንደሚገኝ አሰታወቋል፡፡

በዚህ ሁኔታ ዉስጥ የሚገኘዉ ክሪሚሊን ምእራባዉን ናቸዉ ይሕን ሴራ የሚሰሩት በሚል በዋግነር አመጽ ላይ ልዩ ምርመራ መጀመሩን የሀገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ሰርጌ ላቭሮቭ አስታዉቀዋል፡፡

ላቭሮቭ እነዚያ ሁሌም የማይተኙልን ጠላቶቻቸን ትርምስና ቀዉስ ሊጠነስሱሉን ስለሚችሉ ሁኔታዉን በጥንቃቄ እያየን ነዉ ብለዋል፡፡

የሩሲ ፖለቲከኞችም የምእራቡ አለም ሀገራት በተለለይም ዋሽንግተን እጇ ሊኖርበት ይችላል የሚለዉን ጥርጣሬ የነጩ ቤተመንግሰት እኔ ከደሙ ንጹህ ነኝ የሚል መግለጫ አዉጥቷል፡፡

ፑቲን ግን ምእራባዉያኑ ቢያብተለጥሏቸዉም የቅርብ ወዳጆቻቸዉ ኢራንና ቻይና አይዞት ከጎንዎ ነን የሚል መግለጫ መስጠታቸዉን አልጄዚራ ዘግቧል፡፡

በየቭገኒ ፕሪጎዢን የሚመራው ቡድን በሩሲያ የጦር አመራሮች ላይ በይፋ ካመጸ በኋላ፣ ሁለት የሩሲያ ከተሞችን ተቆጣጥሮ ወደ ሞስኮ ሲገሰግስ ነበር።

ይሁን እንጂ የቡድኑ መሪ በቤላሩሱ ፕሬዝዳንት አሸማጋይነት ከፑቲን ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ወደ ሞስኮ የሚያደርጉትን ዘመቻ አቁመዋል።

ሰኔ 20 ቀን 2015 ዓ.ም

በአባቱ መረቀ

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.