በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ከተማ ውስጥ በትናንትናው እለት ጠዋት በደረሰ ከባድ የትራፊክ አደጋ የ10 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ አምስት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።
የአምቦ ከተማ ፖሊስ እንዳስታወቀው፤ ትናንት ሰኞ ሰኔ 19/2015 አደጋው የደረሰው ከአምቦ ወደ ጉደር ሰዎችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ በነበረ ፋይፍ ኤል በሚባል ሚኒባስ መኪና ላይ ነው።
አደጋው የደረሰው ጠዋት ሦስት ሰዓት ላይ ተልተሌ በሚባል ስፍራ ሲሆን፣ ሚኒባስ ተሽከርካሪው በከፍተኛ ፍጥነት ዩሮ ትራከር ከተባለ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ መሆኑን የአምቦ ከተማ ትራፊክ ፖሊስ ባልደረባ ረዳት ኢንስፔክተር እመቤት ተሾመ መናገራቸውን የከተማው ኮምዩኒኬሽን ገልጿል።
ለአደጋው ምክንያት ፋይፍ ኤል ተብሎ የሚታወቀው ሚኒባስ ከቁጥጥር ውጪ በመሆኑ እንደሆነ የትራፊክ ፖሊስ ባልደረባዋ አመልክተው፤ አሽከርካሪዎች መንገድ ከመጀመራቸው በፊት የመኪኖቻቸው ክፍሎች በአግባቡ እንደሚሰሩ መረጋገጥ እና ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያ
ሰኔ 20 ቀን 2015 ዓ.ም











