እስራኤል ግዙፍ የአውሮፕላን ጥገና ማዕከል በኢትዮጵያ እንደሞትከፍት አስታወቀች፡፡

የእስራኤሉ ኤሮስፔስ የመንገደኛ አውሮፕላኖችን ወደ ጭነት ማጓጓዣ መቀየር የሚያስችል የጥገና ማዕከል በኢትዮጵያ እንደሚከፍት የሀገሪቱ ኢምባሲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለሊ አድማሱ ከጣቢያችን ጋር ባደረጉት ቆይታ ፣ የመንገደኛ አውሮፕላኖችን ወደ ካርጎ ወይንም ጭነት አገልግሎት ለመቀየር የሚያስችል ግዙፍ የጥገና ማዕከል በቅርቡ ይከፈታል ብለዋል።
የእስራኤሉ እሮስፔስ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር ሶስት የመንገደኛ አውሮፕላኖች
የጭነት አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻሉንም አምባሳደሩ ተናግረዋል።

በቀጣይ እስራኤል ግዙፍ የአውሮፕላን ጥገና ማዕከል በኢትዮጵያ በመክፈት ለሌሎች ሀገራት አየር መንገዶች አገልግሎት እንደምሰጥ ታውቋል።
የእስራኤሉ ኤሮስፔስ በኢትዮጵያ የሚከፍተው የአውሮፕላን ጥገና ማዕከል በአለም ላይ ያለውን ቁጥር ወደ አራት ከፍ ያደርገዋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመንገደኞች ብቻም ሳይሆን በጭነት አገልግሎት ውጤታማ መሆኑን የገለጹት አምባሳደር አለሊ፣በቀጣይ ከዚህ የበለጠ ደረጃ ላይ ለማድረስ እስራኤል ከአየር መንገዱ ጋር በትብብር ትሰራለች ነው ያሉት።

የእስራኤሉ ኤሮስፔስ በአቪዬሽን ዘርፍ ስመጥር ተቋም መሆኑ ይነገርለታል።

በአባቱ መረቀ

ሰኔ 20 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *