የሴራሊዮን ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ የሀገሪቱን ምርጫ ጊዜያዊ ውጤት እንደማይቀበለው አስታወቀ፡፡

በሴራሊዮን በምርጫ እየተሰታፈ የሚገኘውና የሀገሪቱ ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ ጊዚያዊ ፕሬዝዳናታዊ ምርጫ ውጤቱን እንደማይቀበለው አስታውቋል፡፡
ጊዚያዊ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ ባዮ እየመሩት እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡

የቅዳሜውን ምርጫ ተከትሎ የ59 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ማዳ፣ ምርጫውን እየመሩ መሆኑ ከተነገረ በኃላ በሀገሪቱ ውጥረት ነግሷል፡፡
የመላው ህዝባዊ ኮንግረንስ /ኤ ፒ ሲ/ ፓርቲ ዋና እጩ የሆኑት የ72 ዓመቱ ሳሙራ ካማራ ዋነኛ ተፎካካሪ ናቸው፡፡

በትናንትናው እለት የወጣው የፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ውጤት እንደሚያሳየው፣ ካማራ 8 መቶ ሺህ ድምፅ በማግኘት ሲከተሉ ፕሬዝዳንት ባዮ አንድ ሚሊዮን ድምፅ በማግኘት ምርጫውን እየመሩ እንደሚገኝ ተገልፃል፡፡

ኤ ፒ ሲ ባወጣው መግለጫ የምርጫ ቦርድ ይፋ ያደረገው ጊዚያዊ ውጤትን ፈፅሞ እንደማይቀበልና የተቀነባበረ የመርጫ ውጤት ነው ብሎ እንደሚያምን አስታውቋል፡፡

ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች እንዳስታወቁትም የምረጫው ውጤት ቆጠራው ግልፀኝነት የጎደለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ካማራ ከዚህ ቀደምም በ2018 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በባዮ መሸነፋቸው የሚታወቅ ነው፡፡
በአቤል ደጀኔ

ሰኔ 20 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.