አሜሪካ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን እንደማትልክ በድጋሜ አስታወቀች፡፡

የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ዩክሬንን ለመርዳት ወታደሮቹን ወደ ስፍራዉ እንደማይልክ የሀገሪቱ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በድጋሜ አረጋግጧል፡፡

ከአሜሪካ በተጨማሪም የአዉሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በተናጠል ወታደሮቻቸዉን ወደ ዩክሬን እንደማይልኩ አስታዉቀዋል፡፡

የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ማቲዉ ሚለር እንዳስታወቁት፤ ከሩሲያ ጋር ለመዋጋት ምንም አይነት ወታደር ወደ ዩክሬን አንልክም ነዉ ያሉት፡፡

ቃል አቀባዩ የአሜሪካን ጨምሮ የምዕራባዉያን ልዩ ኃይሎች በዩክሬኑ አዉደ ዉጊያ አሉ የሚለዉን ክስ ዉድቅ ማድረጋቸዉንም አርቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡

ዋሽንግተን ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን አልክም ትበል እንጅ ለኬይቭ የምታደርገዉን የጦር መሳሪያ ድጋፍ አጠናክራ እንደመትቀጥል ግን አስታዉቃለች፡፡

የአዉሮፓ ህብረት የወታደራዊ ሃይል ምክትል አድሚራል ሄርቭ ብሌጀን ምእራባዉያን ወታደሮቻቸዉን ወደ ዩክሬን ካሰማሩ አደገኛ እልቂት እንደሚያስከትል አስጠንቅቀዋል፡፡

በአባቱ መረቀ

ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.