ሰዋሰዉ መልቲሚዲያ “ሰዋሰዉ ፖድካስት ኔትወርክን” ወደ ስራ ማስገባቱን በዛሬው እለት ይፋ አደረገ።

የበርካታ ፖድካስቶች ስብስብ እንደሆነ የተነገረለት ሰዋሰዉ ፖድካስት ኔትወርክ ዛሬ ሰኔ 29/2015 ዓ.ም የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት ተቋማት ሀላፊዎች እና ፖድካስተሮች በተገኙበት በዛሬው እለት በይፋ ተመርቋል።

በሙዚቃ ስርጭት ግብይቱ የሚታወቀዉ ሰዋሰዉ መተግበሪያ ከአዋቂ አቅራቢዎች ወይንም ፖድካስተሮች ጋር በመሆን “ሰዋሰዉ ፖድካስት ኔትወርክን” ይፋ አድርገዋል።

ሀሳብ ያለዉ ሃሳቡን፣ተስጥኦ ያለዉ ክህሎቱን የሚስብና አዝናኝና አሰተማሪ የሚሆኑ ፖድካስቶች ይቀርቡበታል ተብሏል።

የሰዋሰዉ የዲጂታል ሙዚቃ ማስተላለፊያ አካል የሆነዉ ሰዋሰዉ ፖድካስት ኔትወርክ ቃጠሎ፣የመኖር ጥበብ፣ቃላት፣የእናት መክሊት፣ታሪክ ይሞግት፣ሌጋል ፕላስ ፖድካስት እና ፕርጀክት አስተዳደር ፖድካስቶች በመተግበሪያዉ መተላለፍ እንደሚጀምሩ የሰዋሰዉ ፕድካስት ኔትወርክ ዋና ሀላፊ አቶ በሀይሉ ተስፋሁን ተናግረዋል።

ሰባት ያህል በህይወት መንገድ ላይ፣መፅሀፍት ላይ፣ሙዚቃ እንዲሁም የህግ ጉዳይና ስለ ህክምና ማወቅ የሚቻልበት የመረጃ ምንጭ መሆኑንም ገልፀዋል።

በማስጀመሪያዉ መርሐ ግብር ላይ የተገኙት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ዴኤታ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ “ሀገራችን እየተቸገረችበት ላለዉ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ላይ እየደረሰ ያላዉን ቀዉስ ለመፍታት እንደዚህ አይነት ሀላፊነት የሚሰማቸዉ ተቋማት የሚበልፅጉ መተግበሪያዎችን” መንግስታቸዉ የሚደግፈዉ መሆኑን ተናግረዋል።

መርሀ ግብሩ ሰፋ ያለ የፓናል ዉይይት የተካሄደበት ሲሆን የመወያያ ሀሳቡም የፖድካስት ሚዲያ እምቅ አቅምና አስተዋፅኦ” በሚል ርዕስ የፓናል ዉይይት ተካሂዷል።

ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር የስራ፣ስራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በበኩላቸዉ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር የሙዚቃዉን ኢንዲስትሪ ለማገዝ ከሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት ጋር በመሆን እየሰራ ሲሆን ሰዋሰዉ እየሰራ ያለዉ ስራ ሀገርን ከማሰታዋወቅም ባሻገር፣ ለበርካታ ስራ ፈላጊዎች የስራ ዕድል እየፈጠረ ያለ ተቋም በመሆኑ ቢሯቸዉ አብሮ ለመስራት ሁሌም ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የመግስት አካላት እንዲሁም የሰዋሰዉ ሊቀመንበር የሆኑት ወይዘሪት ሳምራዊት ፍቅሩን ጨምሮ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸዉ የሚዲያ አካላት ተገኝተዋል።

ፖድካስት በማንኛውም ቦታ እና ጊዜ በድምፅ ወይም በምስል የሚቀርብ ሀሳብ መለዋወጫ መተግበሪያ ሲሆን ፖድካስት ኔትወርክ የምንለዉ ደግሞ በርካታ ፖድካስቶች አንድ ላይ የሚገኙበት እንደሆነ ተነግሯል።

በአቤል ደጀኔ

ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.