ቅዱስ ሲኖዶስ የሰሜኑ ጦርነት በተካሄደበት ወቅት ጦርነቱ እንዲቆም መግለጫ ባለመስጠቱ እና በወቅቱ በትግራይ ክልል ተገኝቶ ሕዝቡን ባለመጠየቁና ባለማጽናናቱ ይቅርታ ጠየቀ፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ለሁለት ቀናት ያካሄደውን ልዩ ጉባኤ ማጠናቀቁን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሚዲያዎች በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በሁለት ዐበይት አጀንዳዎች መወያየቱን ገልጾ፣ የኤጲስ ቆጶሳትን ሹመት በተመለከተ የተመረጡ ቆሞሳትን ይፋ በማድረግ የፊታችን ሐምሌ ዘጠኝ ሢመቱ እንደሚፈጸም አስታውቋል።

በሌላ በኩል በትግራይ ክልል በተካሄደው ጦርነት ወቅት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን ጦርነቱ እንዲቆም በወቅቱ መግለጫ ባለመስጠቷ፣ በጦርነቱ መካከል ወደ ትግራይ ክልል መግባትና መውጣት በሚቻልበት ወቅትም በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና መላው ሕዝበ ትግራይን በአካል በቦታው ተገኝታ ባለመጠየቋና ባለማጽናናቷ፣ ጦርነቱ ቁሞ በሀገር አቀፍ ደረጃ እርቀ ሰላም ከወረደበት ጊዜ ጀምሮ ለደረሰው ጉዳት በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነውን ሰብአዊ ድጋፍ በውሳኔው መሠረት በወቅቱ ማድረስ ባለመቻሏ፣ በዚሁም የተነሣ በቤተ ክርስቲያኗና በመላው ሕዝበ ትግራይ መካከል ለተፈጠረው ቅሬታና አለመግባባት ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታ መጠየቁን በንባብ ከተሰማው የቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ ለመረዳት ተችሏል።

@ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.