በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራው አሊያንስ ፎር ኤ ግሪን ሪቮሉሽንስ ኢን አፍሪካ / አግራ የኢትዮጵያ ግብርና ለማዘመን 15. 5 ሚሊዮን ዶላር መበጀቱን አስታወቀ::

አሊያንስ ፎር ኤ ግሪን ሪቮሉሽንስ ኢን አፍሪካ / አግራ የኢትዮጵያን ግብርና ለማዘመንና የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ያስችላል ያለውን ዕቅድ በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል ።

ዕቅዱ በቀጣይ አምስት አመታት በኢትዮጵያ እንደሚተገበርም ተነግሯል።

የአግራ ሊቀመንበርና የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፣የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ በትኩረት እንሰራለን ብለዋል።

ይፋ የተደረገው ስትራቴጂ የአነስተኛ መሬት ይዞታ ያላቸውን አርሶ አደሮች አቅም በማሳደግ ምርትና ምርታማነትን እንደሚያሳድግም አቶ ኃይለማርያም አስታውቀዋል።

አግራ በዘርፍ የሚስተዋሉ ቾግሮችን በመፍታት የምግብ ደህንነትን ማስጠበቅና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከለል እንደሚሰራም በመድረኩ ተነስቷል።

በኢትዮጵያ ለሚተገብረው የአምስት አመት ስትራቴጂም 15.5 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት እንዳደረገ በመድረኩ ተነስቷል።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ በበኩላቸው አግራ ይፋ ያደረገው ዕቅድ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።

የግብርናው ዘርፍ 65 በመቶ ለሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ የሥራ ዕድል እንደፈጠረም ሚኒስትር ዴኤታው አስታውቀዋል።

በመሆኑም የግብርናውን ዘርፍ ለማሳደግና የምግብ ዋስትናን ለማረጋጠጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ ተጠይቋል።

አግራ እ.ኤ.አ በ2006 የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጥምረት በሚል መመስረቱ የሚታወስ ነው።

በአባቱ መረቀ

ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.