የሃራሪ ክልል 65 በመቶ የማመርተው ውሃ በሃይል መቆራረጥ ምክንያት ለነዋሪው እየደረሰ አይደለም ብሏል።

የሃረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ቢሮ 65 በመቶ የማማርተው ውሃ በሃይል መቆራረጥ ምክንያት ለነዋሪው እየደረሰ አይደለም ሲል ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል ።

ታሪካዊቷ የሃረር ከተማም በከፍተኛ የውሃ ችግር ውስጥ እንደምትገኝ የገለፀው ቢሮው በድሬዳዋ የሚመረተው የንፁህ መጠጥ ውሃ ወደ ከተማዋ ለማድረስ መቸገሩን ገልጿል።

የክልሉ የውሃና ፍሳሽ ቢሮ የቴክኒክ እና ኦፕሬሽን ስራ ሂደት ኃላፊ አቶ ሃድሊ በክሪ መሃመድ በክልሉ በዚህ አመት ውሃ በአማካይ ለ99 ቀናት መቋረጡን ለጣቢያችን ተናግረዋል።

ኃላፊው አክለውም በሃረር ከተማ ውሃ በወር ውስጥ የሚጠፋበት አማካይ ጊዜ ከ15 ቀን ወደ 20 ቀን ከፍ ማለቱን ገልጸዋል።

ከድሬዳዋ ተመርቶ ወደ ሃረር የሚገባው ውሃ 1ሺህ ሜትር ኪውብ መሆኑን ያነሱት ሃላፊው በኃይል መቆራረጥ ምክንያት ወደ ከተማው የሚገባው 30 በመቶ ብቻ ነው ብለዋል።

ከሃይል መቆራረጥ የተነሳ ካሉት አራት የውሃ ማከማቻ ፓምፖች ሁለቱ መቃጠላቸው ደግሞ በክልሉ የሚስተዋለውን የውሃ ችግር እንዳባባሰው ገልጸዋል።

ከሃይል መቆራረጡ በተጨማሪ በሃረር ከተማ ከመሬት አቀማመጥ ጋር ተያይዞ ውሃ የማይደርስባቸው ቦታዎች እንዳሉ አንስተዋል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍ በፌዴራል መንግስት ተደጋጋሚ ቃሎች ቢገቡም ተጨባጭ መፍትሔ ግን ማምጣት አለመቻሉን ኃላፊው ተናግረዋል።

በመሳይ ገ/መድህን

ሐምሌ 06 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.