የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዳይሬክተር ጂማ ዲልቦ በፈቃዳቸው ከኃፊነታቸው ለቀቁ::

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጂማ ዲልቦ በገዛ ፈቃዳቸው ስራቸውን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል።

ዳይሬክተሩ ከአራት ዓመታ በላይ ከመሩት ተቋም ስራቸውን ለመልቀቅ ያቀረቡት ጥያቄ በመንግስት ተቀባይነት ማግኘቱን ተናግረዋል። የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ኃላፊ ስራቸውን ለምን እንደለቀቁ ያሉት ነገር የለም።

ጂማ ዲልቦ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ “ዘርፉ ከነበረበት ድባቴ ወጥቶ ለሀገር ልማትና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ አስተዋጽኦ ማበርከት መጀመሩ በቀጣይ ዓመታት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ተሻሽሎ ተቋሙ ዳግም ሲደራጅ ጀምሮ ነበር በኃላፊነት ላይ የነበሩት።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 06 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.